Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

‎አረንጓዴ ዐሻራ ዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገውን ትውልድ ታሳቢ አድርጎ እየተተገበረ ነው – አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ‎የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገውን ትውልድ ታሳቢ በማድረግ እየተተገበረ ነው አሉ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ ‎የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን በአሶሳ ዞን ዑራ ወረዳ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡

በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በክልሉ 80 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱ ተገልጿል።

አቶ አሻድሊ ሀሳን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ‎መርሐ ግብሩ በክልሉ የደን ሽፋንን ከማሻሻል ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ ውጤቶች አስገኝቷል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በዓለም አቀፍ መድረክ አርዓያ የሚሆን ተግባር አከናውናለች ነው ያሉት፡፡

አረንጓዴ ዐሻራ የለውጡ መንግስት የተሻለች አረንጓዴ ሀገር ለትውልዱ የማስረከብ ቁርጠኝነት ማሣያ መሆኑን ገልጸው፥ ዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገውን ትውልድ ታሳቢ አድርጎ እየተተገበረ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

Exit mobile version