Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአማራ ክልል በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የገበያ ማዕከላት እየተገነቡ ነው

‎አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ በክልሉ ሰባት ዞኖች ውስጥ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ እየተካሄደ ነው አለ።
የቢሮው ኃላፊ ኢብራሂም መሀመድ (ዶ/ር)፤ በ2017 ዓ.ም በስምንት ከተሞች በ1 ነጥብ 37 ቢሊየን ብር ወጪ ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን አስታውሰዋል።
ማዕከላቱ ሸማቹ ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የኢንዱስትሪና ግብርና ምርቶችን እንዲያገኝ ዕድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል።
ዘንድሮ በሰባት የዞን ከተሞች የገበያ ማዕከላት ግንባታ እየተካሄደ እንደሆነ አንስተው፤ በክልሉ መንግሥት 500 ሚሊየን እንዲሁም ከተሞቹ 800 ሚሊየን ብር የተቀናጀ በጀት የማዕከላቱ ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑን ተናግረዋል።
በፍኖተሳለም፣ እንጅባራ፣ ደባርቅ፣ ገንዳውሃ፣ ሁመራ፣ ሰቆጣና ከሚሴ ከተሞች እየተገነቡ ያሉት ማዕከላቱ በተያዘላቸው ጊዜ በፍጥነትና በጥራት እንዲጠናቀቁ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።
የመንግሥት የልማት ድርድቶች በፕሮጀክቶች ግንባታ መሳተፋቸው በውስን በጀት የተሻለ ስራ ለመፈፀም ማስቻሉን ተናግረዋል።
በምናለ አየነው
Exit mobile version