Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ አዲስ የተሾሙ የ11 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡

የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንቱ ያቀረቡት የሳኡዲ አረቢያ፣ የኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ፖርቹጋል፣ ናይጄሪያ፣ ስሪላንካ፣ ማላዊ፣ ጋና፣ ኡራጓይ፣ ስሎቫኪያ፣ ማዳጋስካር እና ኡዝቤኪስታን አምባሳደሮች መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

Exit mobile version