አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ከማሌዥያ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች አሉ።
የማሌዥያው ጠቅላይ ሚኒስትር ብልጽግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማሸነፉን አስመልክቶ ላስተላለፉት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ (ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል።
በምስጋና መልዕክታቸው ኢትዮጵያ እና ማሌዥያ በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ያላቸው እና የደቡብ ለደቡብ ትብብር ራዕይን የሚጋሩ ሀገራት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከማሌዥያ ጋር ያላትን የጋራ ትብብር ለማጠናከር እንደምትሰራም አረጋግጠዋል፡፡
የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ማሌዥያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ለምታደርገው ትብብር ኢትዮጵያ አስፈላጊ መሆኗን በመግለጽ÷ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት መናገራቸው ይታወሳል።

