Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሴኔቱ የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይሎች ከኢራን ጦርነት እንዲወጡ የሚያስችል ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ሴኔት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱን ወታደራዊ ሀይሎች ከኢራን ጦርነት እንዲያስወጡ የሚያዘውን ውሳኔ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

የውሳኔ ሀሳቡ የተላለፈው የአሜሪካ እና የኢራን ተደራዳሪዎች ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በስዊዘርላንድ እየተወያዩ ባለበት እና በቴክኒካል ድርድሮች ላይ ከስምምነት በደረሱበት ወቅት ነው፡፡

ውሳኔው በስዊዘርላንድ እየተካሄደ ያለው ድርድር ባይሳካ ሀገሪቱ ተመልሳ ወደ ጦርነት እንዳትገባ እና ለኢራን ጦርነት ተልዕኮ የተሰማራው ወታደራዊ ኃይል በአስገዳጅነት ከአባቢው እንዲወጣ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከ50 የሴኔቱ አባላት 48ቱ ውሳኔውን በድምፅ የደገፉ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ከሚመሩት የሪፐብሊካን ፓርቲ አራት ሰዎች ፕሬዚዳንቱ ወታደራዊ ኃይላቸውን ከኢራን እንዲያስወጡ የሚያዘውን ውሳኔ ደግፈዋል ተብሏል፡፡

እንደ አር ቲ ዘገባ፤ ውሳኔው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራንን በተመለከተ የሚከተሉት ፖሊሲ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ቀደም ሲል የዴሞክራቲክ ፓርቲ የሴኔት አባላት ከኢራን ጋር የሚደረገውን ጦርነት ፕሬዚዳንቱ እንዲያስቆሙ ለማድረግ ከአስር ጊዜ በላይ ጥያቄ ቢያቀርቡም በቂ ድጋፍ ባለማግኘቱ ሳያሳካ ቀርቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአሜሪካ ሴናተሮች የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ጥረቴን እያከበዱብኝ ነው ሲሉ ገልፀው፤ ውሳኔ የዘገየ እና ትርጉም አልባ ነው ማለታቸውን ዘገባው ጠቁሟል።

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version