አዲሰ አበባ፤ ሰኔ 18፤ 2018 ዓ.ም (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ አንጉቲ ቀበሌ አስጀምረዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

