Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ብልጽግና ፓርቲ ለሕዝብ የገባውን ቃል ለመፈጸም ቁርጠኛ ነው – አቶ ፍቃዱ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል ተቋማት ብልጽግና የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሥራዎች ማጠቃለያ መድረክ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ እንዳሉት÷ በምርጫው ፓርቲው ያስቀመጣቸውን ግቦች አሳክቷል።

የፌዴራል ተቋማት አመራሮች ምርጫውን በማስተባበር፣ ክርክሮች ላይ በንቃት በመሳተፍ፣ ለክልሎች ድጋፍ በማድረግ ውጤታማ ሥራ ማከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

አመራሮቹ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የነበራቸው የነቃ ተሳተፎ ፓርቲው ግቡን እንዲያሳካ ሚናቸው የጎላ መሆኑን አመልክተዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ ለሠላም፣ ለልማትና ለዴሞክራሲ መጠናክር ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የፓርቲው አመራሮች ከድል ማግስት እምነቱን አሳድሮ ይሁንታውን ለሰጣቸው ሕዝብ የተቀበሉትን አደራ በትጋት መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

አቶ ፍቃዱ ነገን ተስፋ በማድረግ ለመረጠው ሕዝብ ብልጽግና ፓርቲ በማኒፌስቶው የገባውን ቃል ለመፈጸም ቁርጠኛ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በአንዱዓለም ተስፋዬ

 

Exit mobile version