አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ ሕወሓት እየፈጸመ ያለው አስገዳጅ የወታደራዊ ምልመላ እንቅስቃሴ የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚጥስ ነው አለ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ፡፡
የኅብረቱ ልዑክ ባወጣው መግለጫ ቡድኑ በቅርብ ጊዜያት የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በኃይል በማስወገድ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እያደረገ መሆኑን አመልክቷል፡፡
እነዚህ እንቅስቃሴዎች የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የሚጥሱ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
አሜሪካ የቀድሞው ህወሓት መሰል የጥፋት ተግባራት እየፈጸመ መሆኑን በመግለጽ፥ በቡድኑ ጽንፈኛ አመራሮችና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ በቅርቡ የቪዛ እገዳ መጣሏ ይታወሳል፡፡

