Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የ32ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቅቀዋል።

ከየምድቦቻቸው 1ኛ እና 2ኛ በመሆን 24 ሀገራት በቀጥታ እንዲሁም ተጨማሪ 8 ሀገራት ምርጥ 3ኛ በመሆን የ32ቱን ጥሎ ማለፍ ተቀላቅለዋል።

በዚህም መሰረት የ32ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ከምድብ 1 እና 2 ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቁት ደቡብ አፍሪካ እና አዘጋጇ ሀገር ካናዳ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል።

ምድብ ሦስትን በበላይነት ያጠናቀቀችው ብራዚል ከጃፓን እንዲሁም የምድብ 5 አሸናፊዋ ጀርመን ከፓራጓይ ተደልድለዋል።

ኔዘርላንድስ ከሞሮኮ፣ ኮትዲቯር ከኖርዌይ፣ ፈረንሳይ ከስዊድን፣ ሜክሲኮ ከኢኳዶር፣ እንግሊዝ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ እንዲሁም ቤልጂዬም ከሴኔጋል ይገናኛሉ።

አሜሪካ ከቦሲኒያ ሄርዞጎቪና፣ ስፔን ከኦስትሪያ፣ ፖርቹጋል ከክሮሺያ፣ ስዊዘርላንድ ከአልጄሪያ፣ አውስትራሊያ ከግብጽ፣ አርጀንቲና ከኬፕቨርዴ እንዲሁም ኮሎምቢያ ከጋና ተደልድለዋል።

Exit mobile version