Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በፈረንሳይ በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምስራቅ ፈረንሳይ ቶምብላይን ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ አብራሪውን ጨምሮ የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

ለአንድ ፓራሹት ማሰልጠኛ ት/ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ሲቭል አውሮፕላን ከናንሲ ኢሴይ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ብዙም ሳይቆይ መከስከሱ ተመላክቷል፡፡

በተፈጠረው አደጋም አብራሪውን ጨምሮ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ የ11ዱም ሰዎች ሕይወት ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከሟቾች መካከል አምስቱ የትምህር ቤቱ ተማሪዎች ሲሆኑ ÷ አምስቱ ደግሞ መምህራን እንደነበሩ ተጠቁሟል፡፡

የፈረንሳይ ትራንስፖርት ሚኒስቴር በተከሰተው አሰቃቂ አደጋ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ ÷ የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

Exit mobile version