Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀገርን መልክ እያሳየ የሚገኘው አረንጓዴ ዐሻራ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር መንግሥቱ በቀለ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሀገርን መልክ እያሳየ ነዉ አሉ።
የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በዛሬው ዕለት ይፋ እየተደረገ ነው።
በምዕራብ አርሲ ወንዶ ወረዳ ጎቱ ኦኖማ ቀበሌ የተገኙት ዶክተር መንግሥቱ በቀለ እንዳሉት፤ መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያ የሚገባትን መልክ እየገለጠ ይገኛል።
ሀገሪቱ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ለመጠቀም ዕድል በመፍጠሩ ትክክለኛ መልኳን እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።
የመርሐ ግብሩ ባለፉት ዓመታት መተግበር የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ እንደሚገኝ ገልጸው፤ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም እያስቻለ መሆኑንም አንስተዋል።
በተጨማሪም የውሃ ሃብት አቅምን እንዲጎለብት ማድረጉንም ጠቅሰዋል።
ዘንድሮ በኦሮሚያ ክልል 5 ነጥብ 3 ቢሊየን ችግኞች የተዘጋጁ ሲሆን፤ ምዕራብ አርሲ ዞን 275 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ማድረጉ ተገልጿል።
በዚህም 65 ሺህ ሄክታር መሬት ተለይቷል።
በዞኑ ከሚተከሉት ችግኞች 40 በመቶ የሚሆኑት የደን፣ 10 በመቶ የፍራፍሬ፣ 25 በመቶ የእንስሳት መኖ እንዲሁም 25 በመቶ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች ናቸው።
በጌታቸዉ ሙለታ
Exit mobile version