Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያና ጣሊያን የ70 ሚሊየን ዩሮ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የ70 ሚሊየን ዩሮ የብድር ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል፡፡

የብድር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ሴም ፋብሪዝ ተፈራርመውታል።

አሕመድ ሽዴ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ በረጅም ጊዜ የሚከፈለው የብድር ስምምነቱ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የልማት ሥራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነት የሚያሳይና የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ የሚያጠናክር አንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱ ቀደም ሲል በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሱት የትብብር ማዕቀፎች አካል እንደሆነ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ ኢትዮጵያ የጀመረቻቸውን ሀገራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ርምጃዎችና የልማት ግቦችን ለማሳካት አስተዋፅዖ እንደሚኖረው አስረድተዋል።

የጣሊያን መንግሥት ለኢትዮጵያ የልማት ጥረቶችና የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍና ቀጣይነት ላለው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል።

Exit mobile version