የቀድሞው ሕወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን አዳዲስ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ለውጦች ተቀብሎ ራሱን ማደስ አልቻለም፡፡
በዚህ ዘመን ላይ ሆኖ ለአዲሱ ትውልድ የድሮውን አብዮታዊ ዴሞክራሲ መዘመር ያስባል፡፡
ይህ አካሄድ የቡድኑን ራስን ከማደስ ወደ ራስን ማጥፋት መሸጋገር ያሳያል፡፡
የስብስቡ ግትር አስተሳሰብ፣ በሥልጣን ላይ ባለበት ጊዜ እንኳን ከሌሎች የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር በጋራ መሥራት ላለመቻሉ ምስክር ነው፡፡
ቡድኑ ይህንን አጥፊ የፖለቲካ አዙሪት ሰብሮ መውጣት አልቻለም፡፡
ውስጣዊ ዴሞክራሲን ቢያሰፍን፣ አዲስ አመራር እና አስተሳሰብ ቢተካ፣ እንዲሁም ለሰላምና ለሕግ የበላይነት ሙሉ በሙሉ ተገዢ ቢሆን የመዳን ዕድል ይኖረው ነበር፡፡
ነገር ግን የቀድሞው ሕወሓት የፖለቲካ ጉዞ ሲገመገም፣ ድርጅቱ ካለፉት ታሪካዊ ስህተቶቹ ታርሞ ራሱን ከማደስ ይልቅ፣ ሁልጊዜ ወደ አጥፊ የፖለቲካ አዙሪት ውስጥ የመመለስ ልምምድ ይታይበታል።
ይህ አዙሪት ራሱን ብቻ ሳይሆን የትግራይን ሕዝብ እና መላዋን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ይገኛል።
ስብስቡ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ከፖለቲካ አዙሪቶች መውጣት አልቻለም፡፡
የቀድሞው ሕወሓት መሠረታዊ የሐሳብ ልዩነቶችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከማስተናገድ ይልቅ፣ መከፋፈል እና አንዱ ሌላውን የመደፍጠጥ ልምምድ አለው።
ካለፉት የታሪክ ስህተቶቹ አለመማሩን የሚያሳየው፣ ከሰሜኑ ጦርነት ማብቃት በኋላ እንኳን የተፈጠረውን የሰላም አየር ለማስቀጠል አለመፈለጉ ነው፡፡
ቡድኑ ጊዜያዊ አስተዳደሩን አፍርሶ በትግራይ እና በክልሉ ልሂቃን መሀከል የፈጠረው ፍጥጫ፣ አሁንም በሥልጣን ሽኩቻ አዙሪት ውስጥ መታሰሩን ያሳያል።
የቀድሞው ሕወሓት የፖለቲካ ጥያቄዎችን እና አለመግባባቶችን በሰላማዊ ውይይት ከመፍታት ይልቅ፣ ወደ ኃይል አማራጭ የመግባት አባዜ አለበት።
በ2013 ዓ.ም የተቀሰቀሰው አውዳሚ የሰሜኑ ኢትዮጵያ ጦርነት የዚሁ ቡድን እኩይ የአስተሳሰብ ውጤት ነበር።
ከጦርነቱ በኋላ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለአካባቢው አንጻራዊ ሰላም ቢያመጣም፣ በስብስቡ ውስጥ ያሉ አካላት አሁንም ጊዜ ካለፈበት የትጥቅ ትግል ስነ-ልቦና መውጣት ባለመቻላቸው አዙሪቱን አስቀጥሎታል፡፡
ቡድኑ የሥልጣን ወይም የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ፣ የትግራይን ሕዝብ “የህልውና አደጋ ተጋርጦብሃል” በሚል ስጋት ውስጥ መክተት ዋነኛ መሣሪያው ነው።
የራሱን ስልታዊ እና ፖለቲካዊ ስህተቶች በሙሉ ከውጭ የመጣ ጥቃት አስመስሎ በማቅረብ፣ ከሕዝብ የሚነሳበትን የተጠያቂነት እና የለውጥ ጥያቄ ያፍናል።
የዓለም እና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየሩ ቢሆንም፣ የቀድሞው ሕወሓት ግን አሁንም የ1960ዎቹ አስተሳሰብ ላይ ተቸንክሮ ቆሟል፡፡
አብዮታዊ ዴሞክራሲ አሁንም ህልሙ ነው፡፡
ይህ ዓይነቱ ግትርነት ከሌሎች የሀገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች ነጥሎታል፡፡
ቡድኑ ከአዙሪት እንዲወጣ ከውስጥም ከውጪም ተመክሯል፡፡
የፖለቲካ አዙሪቱን ሊሰብርለት የሚችለው ስብስቡ ካለፈው ስህተቱ ተምሮ ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ዘመናዊ አስተሳሰብን ሲቀበል ብቻ ነው።
አሁንም ግን ይህንን ማድረግ ባለመቻሉም የቆየው የጥፋት ዑደት ራሱን ወደ ማጥፋት እየወሰደው ይገኛል፡፡
የቀድሞው ሕወሓት የፖለቲካ አዙሪት ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በተመሳሳይ የፖለቲካ ቀውሶች፣ ግጭቶች እና ውስጣዊ መከፋፈሎች ውስጥ በተደጋጋሚ የሚመላለስበትን ሂደት ያሳያል።
ይህ አዙሪት ቡድኑ ከለውጦች ጋር መላመድ አለመቻሉን እና የቆዩ ስልቶችን ደጋግሞ ለመጠቀም መሞከሩን ያመለክታል።
የፖለቲካ አዙሪቱ ካለፉት አምስት አሥርት ዓመታት ጀምሮ በስህተት ላይ ስህተት የሚደጋገምበት ሆኖ ቀጥሏል።
ለዚህ አደገኛ የፖለቲካ ዑደት ዋና ምክንያቶች ድርጅታዊ አፈጣጠሩ፣ ርዕዮተ-ዓለማዊ ሀሳቡ እና ከጊዜው ጋር አብሮ አለማደጉ ናቸው።

