አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ዋንጫ የ32ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ፓራጓይ የ4 ጊዜ የመድረኩን ባለክብር ጀርመን ሳትጠበቅ በማሸነፍ 16ቱን መቀላቀል ችላለች፡፡
ደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ትናንት ምሽት ጀርመንን በመለያ ምት 4 ለ 3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏ ይታወቃል፡፡
ድሉን ተከትሎ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳንቲያጎ ፔና የዛሬው ዕለት የፓራጓይ ብሔራዊ የድል በዓል እንዲሆን አዋጅ አስተላልፈዋል፡፡
ፓራጓይ በቀጣይ ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ከፈረንሳይ እና ስዊድን አሸናፊ ጋር በአሜሪካ ፊላደልፊያ ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡

