Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተፈጥሮ ሀብቶችን ለመመዝገብ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዕትም የመሬት አካውንታንት መግለጫ ሪፖርትና የተፈጥሮና አካውንቲንግ ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆኗል።

ፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከዓለም ባንክን እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጀው ይህ ፍኖተ ካርታ ውሃ፣ ካርቦን፣ ስህነ ምህዳርና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶችን ለመመዝገብ ያስችላል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሃፂዮን÷ ፍኖተ ካርታው ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ተያይዞ የሚተገበር መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም የተፈጥሮ ሀብቶችን መመዝገብ እንደቻል ጠቅሰው÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለው የመሬት መረጃ አመዘጋገብ አቅም እንዲጠናከር ያደርጋልም ነው ያሉት።

በተጨማሪም የተፈጥሮ ካፒታል ካርታዎችን በማደራጀት ከተለያዩ ዘርፎች ጋር በማስተሳሰር ወደ ሀገራዊ ፕላን ለማሳደግ ያስችላል ብለዋል።

ሀገራዊ ፕላን፣ የበጀትና ስታቲስቲክስ ስርዓት ውስጥ ለማካተት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ መመሪያ መሆኑንም አመላክተዋል።

የዓለም ባንክ ኦፕሬሽናል ማናጀር የሆኑት ጁሊያን ቪክቶር በበኩላቸው÷ ፍኖተ ካርታው በመሬት ላይ ያለውን የሀብት አመዘጋገብ ሂደት የሚያዘምን እንደሆነ ገልጸዋል።

የምዝገባ ተግባሩ የአንድ ግዜ ስራ ባለመሆኑ በቀጣይ ተመሳሳይ የመሬት ምዝገባ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ዓለም ተቋማቸው ድጋፉን እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል።

መሬት ሁሉንም አጠቃልሎ የያዘ ሀብት በመሆኑ የአመዘጋገብ ስርአትን በማዘመን ዕድገትን ማሳለጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

እዮናዳብ አንዱዓለም

Exit mobile version