Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፖርቹጋል ከክሮሺያ ፤ ስፔን ከኦስትሪያ…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ እየተካሄደ በሚገኘው 23ኛው የዓለም ዋንጫ የ32ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡

በዚህ መሰረትም የአንድ ጊዜ የመድረኩ ሻምፒዮን ስፔን ምሽት 4 ሰዓት ላይ ከኦስትሪያ ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡

ምድቧን በበላይነት እየመራች ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለችው ስፔን ለዋንጫው ቅድመ ግምት ካገኙ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል አንዷ ናት፡፡

ተጋጣሚዋ ኦስትሪያ በበኩሏ ከምድቧ በአራት ነጥብ ሁለተኛ ሆና ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏ ይታወሳል፡፡

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች አሸናፊ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለመግባት በሚደረገው ፍልሚያ ከፖርቹጋል እና ክሮሺያ አሸናፊ ጋር ይጫወታል፡፡

የጥሎ ማለፍ ጨዋታው ሲቀጥል ሌሊት 8 ሰዓት ላይ ፖርቹጋል ከክሮሺያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ከየምድባቸው ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸው አይዘነጋም፡፡

የጨዋታው አሸናፊ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለመግባት ከስፔን እና ኦስትሪያ አሸናፊ ጋር የሚገናኝ ይሆናል፡፡

በሌላ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ስዊዘርላንድ ከአልጄሪያ ነገ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡

Exit mobile version