Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀሳብ ልዩነት ቢኖርም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት ይገባል – የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀሳብ ልዩነት ቢኖርም በሀገራዊ ጉዳዮቻችን ላይ በጋራ መስራት ይገባል አለ የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት።

የጋራ ምክር ቤቱ በሸገር ከተማ አስተዳደር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አካሂዷል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የተሳተፉ የምክር ቤቱ አባላት እንዳሉት፥ እንደ አረንጓዴ ዐሻራ ያሉ ሀገራዊ ጉዳዮች የአንድ አካል ብቻ ባለመሆናቸው ሁሉም መሳተፍ ይጠበቅበታል።

ከተባበርን እንደ ሀገር የምንፈልጋቸው ስኬቶች ቅርባችን ናቸው ያሉት አባላቱ፥ በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ መተባበር ለነገው ትውልድ የተሻለች ሀገር የመገንባት ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ባለፉት የለውጥ አመታት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በሚልኪያስ አዱኛ

Exit mobile version