Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ተግባራት እየተከናወኑ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተመለከቷቸው የግብርና እና የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ናቸው አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርባ ምንጭ ከተማ የፍራፍሬ ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ግንባታ መጀመራቸውን ጠቁመው ፥ ፋብሪካዎቹ ሲጠናቀቁ የፍራፍሬ ጭማቂ መጠጦችን ለመላክ ያስችላሉ ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በከተማዋ የተገነቡ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ከጥሬው ይልቅ የተቀነባበሩ ምርቶችን ለመላክ እድል ይሰጣል ነው ያሉት፡፡
በግብርናው ዘርፍ የተገኘው ውጤትና ወደ አግሮ ፕሮሰሲንግ የመውሰድ ሒደት በጣም ተስፋ ሰጪ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በግብርና፣ በገጠር ኮሪደር እና የፍራፍሬ ምርትን ከአግሮ-ኢንዱስትሪ ለማስተሳሰርና እሴት ለመጨመር እየተደረጉ ያሉ ሙከራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
በሌላ በኩል በተያዘው ዓመት ኢንዱስትሪው በሀገር ውስጥ የተለያዩ ምርቶችን በማምረት 5 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማዳን መቻሉን ጠቅሰዋል።
በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንኦት የሰጡት፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በጋሞ ዞን የሚገኘውን ‘ዮ ሆልዲንግ’ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ የሥራ እንቅስቃሴ መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡
Exit mobile version