አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች የላሊበላ ቅርሶች ዘላቂ ልማት ፕሮጀክትን ይጎበኛሉ።
በቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ የተመራ ቡድን ላሊበላ ከተማ የገባ ሲሆን፤ ተቀጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በቡድኑ ውስጥ ይገኙበታል።
ቡድኑ በላሊበላ ቆይታው የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናትንና የተለያዩ ስፍራዎችን ከመጎብኘት ባለፈ፤ የላሊበላ ቅርሶች ዘላቂ ልማት ፕሮጀክት አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ ይመለከታል።
የላሊበላ ቅርሶች ዘላቂ ልማት ፕሮጀክት ለጎብኚዎች የሚሆን መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ የሚያተኩር ሲሆን አስቸኳይ የቅርስ ጥገናን ያካትታል።
የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት በዓለማችን ከፍተኛ ተጓዦች ከተመረጡ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ምርጥ አምስት ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ይታወቃል።
በዓለምሰገድ አሳዬ

