አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ውስጥ ለዘረጋው የአየር ትሥሥር እና አብሮ የመሥራት ጥምረቶች ተሸላሚ ሆኗል፡፡
አየር መንገዱ በ2026 የአቪዬሽንና ቱሪዝም ሽልማት ሥነሥርዓት ላይ የ‘ኮኔክቲቪቲ አዋርድ’ ሽልማት ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤር ትራንስፖርት የተበረከተለት ሽልማት በአፍሪካ ውስጥ ለዘረጋው የአየር ትሥሥርና አብሮ የመሥራት ጥምረቶች ዕውቅና ለመስጠት ያለመ ነው፡፡

