Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በፈረንሳይ በከፍተኛ ሙቀት ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንሳይ በአሁኑ ወቅት በተከሰተው ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

በሙቀቱ ምክንያት የተከሰተው የሞት አደጋ ካለፈው ሳምንት አንጻር በ29 በመቶ እንዳሻቀበ የፈረንሳይ ጤና ሚኒስትር ስቴፈን ሪስት ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ እንዳስታወሱት፤ የሙቀት መጠኑ ባለፈዉ ሳምንት 40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነበር።

አሁን ላይ በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች የሙቀት መጠኑ እየጨመረ መጥቷል።

እንደ ቢቢሲ የአየር ትንበያ ዘገባ፤ እየተመዘገበ ባለው የንፋስ እንቅስቃሴ ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ሙቀቱ በአብዛኛው አካባቢ ሊጨምር ይችላል።

እንደ ኮፐርኒከስ የአየር ንብረት አገልግሎት በበኩሉ፤ የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም ዙሪያ የሙቀት መጠኑን እያሳደገ ቢሆንም በአውሮፓ ያለዉ ግን ከሌሎቹ የተለየ ነው ብሏል።

አህጉሩ ፈጣን የሙቀት አማቂ አህጉር በመሆኑ ከዓለም አቀፍ አማካይ የሙቀት መጠን በእጥፍ የሚበልጥ ሙቀት ስለሚሰበስብ ነዉ ሲል አብራርቷል፡፡

በእመቤት ሲሳይ

Exit mobile version