Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ400 ሺህ በላይ ሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደረገው ፕሮጀክት…

የኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት (ኤስኤንቪ) ከመርሲ ኮርፕስ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች እና ወጣቶች የኑሮ ማሻሻያ ሊዌ ፕሮግራምን እየተገበሩ ነው፡፡

ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ የሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሴቶችና ወጣቶች የቅጥርና የራስ ሥራ ፈጠራ ዕድሎችን በማሻሻል ገቢያቸውን ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡

በዚህ መሰረትም ሥራ ቀጣሪና ተቀጣሪን ማገናኘት፣ ለቀጣሪው እና ለተቀጣሪ ምቹና የተሻለ ምሕዳር መፍጠር፣ የስራ ፈጣሪዎች ሥራቸውን እንዲጀምሩ፣ እንዲቀጥሉና እንዲያድጉ መደገፍ ላይ ትኩረት ይደረጋል፡፡

ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች ከሚጠበቀው በታች እያመረቱ የሚገኙ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞችን የአሰራር ሒደትና አቅም በመገንባት የተሻለ ውጤት እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን ተጠቁሟል፡፡

ዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥርዓታዊ መፍትሔዎችንና ጠንካራ አጋርነትን ለማሳለጥ፣ ወጣቶችና ሴቶች ለአካታች የኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ተዋናዮች እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲሁም በገበያ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ አቀራረቦች ዘላቂ የኑሮ መሻሻልን እንዲያመጡ ትኩረት እንደሚያደርግ ተመላክቷል፡፡

ለ5 ዓመታት የቆየው ፕሮግራም የወጣቶችና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በገበያ ሥርአት ልማት ላይ ያተኩር የነበረ ሲሆን÷ በስኬት መጠናቀቁም ተጠቅሷል፡፡

ፕሮግራሙ በቆይታው ከ170 በላይ ከሆኑ የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋሮች ጋር በትብብር መሠራቱና በአሠራር ሥርዓት ላይ ለውጦች መምጣቱ ነው የተገለጸው፡፡

Exit mobile version