👉 ብዙ ሀገራት የንግድ ብድር ተበድረው ደሞዝ ይከፍላሉ፤ እኛ የንግድ ብድር ለልማትም አያስፈልግም ነው ያልነው፡፡
👉 የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ኢትዮጵያ ዕዳ መክፈል አቅቷታል የተባለው የዩሮ ቦንድ ጉዳይ ኢትዮጵያ መክፈል አቅቷት ሳይሆን እነዚያ ዕዳዎች በድርድር መልክ መያዝ አለባቸው የሚል እምነት ስለነበረን ነው፡፡
👉 ተሳክቶልን ዩሮ ቦንድን ጨምሮ ከብዙ አበዳሪዎቻችን ጋር ተስማምተናል፡፡
👉 ኢትዮጵያ የነበረባት ዕዳ ከአጠቃላይ እድገቷ ሲነጻጸር ከ50 በመቶ በላይ ስለነበር ተጨማሪ ብድር ብትወስድ ለመክፈል ትቸገራለች የሚል ክርክር ነበር፡፡ በሰራነው ሪፎርም በአፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ካላቸው ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያ ነው፡፡
👉 የኢትዮጵያ ብድር ከ45 በመቶ በታች ሆኖ ኢትዮጵያ አሁን በምታመነጨው ሀብት ልትከፍል ትችላለች የሚል እምነት በትላልቅ የፋይናንስ ተቋማት እምነት አግኝቷል፡፡
👉 እኛ ያለን ዕዳ አፍሪካ ውስጥ 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ከሚባሉ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት ዕዳ ጋር አይወዳደርም፤ የእነሱ ዕዳ አራት እጥፍ ከእኛ ይበልጣል፤ ብዙዎቹ ቀይ ውስጥ ናቸው፤ እኛ አውርደነዋል፡፡
👉 ይህ በጣም ትልቅ ድል ያገኘንበት ጉዳይ ነው፤ ላለፉት ስምንት ዓመታት ምንም የንግድ ብድር አልወሰድንም፡፡
👉 የሀገር ውስጥ ብድር ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ብድር አገኘሁ ብሎ መውሰድ ሳይሆን ብድር ለመክፈል የሚያስችል ቁመና መኖሩን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡
👉 ከቡድን ሀያ ሀገራት ተስማምተን የሁለትዮሽ እና የዩሮ ቦንድ ስምምነቶች ተፈራርመናል፡፡
በቤተልሔም ግርማ

