Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብዙ ሙያዎች መገኛ ውትድርና …

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ውትድርና የብዙ ሙያዎች መገኛ ነው አሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሕበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት።
ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የመከላከያ ስፖርትና ኪነ-ጥበባት ማዕከልን አጠቃላይ እንቅስቃሴና የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት፤ ማዕከሉ በታሪኩ በርካታ አንጋፋ የሙዚቃና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ለሀገር አበርክቷል።
ይህንን መልካም ስምና ታሪክ ይዞ በመቀጠል አዳዲስ ተተኪዎችን ማፍራት እንደሚገባ ገልጸው፤ ማዕከሉ ለጀመራቸው የመሠረተ ልማት ግንባታዎችና ስራዎች ስኬታማነት የበኩላቸውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርጉም አረጋግጠዋል።
የማዕከሉ ኃላፊ ብርጋዲየር ጀኔራል ጌትነት አዳነ በበኩላቸው፤ ወታደራዊ የኪነ-ጥበብ ስራዎች የነበራቸውን ታሪካዊ ይዘትና አመሠራረት አስረድተዋል።
ተቋሙ በኪነ-ጥበብ ስራዎች በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረኮች በንቃት በመሳተፍ ሀገሩን እያስጠራ እንደሚገኝ መናገራቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል።
Exit mobile version