Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከፖርቹጋል አሰልጣኝነታቸው ተነሱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስፔናዊው አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር መለያየታቸውን የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡

ፖርቹጋል በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የ16ቱ ጥሎ ማለፍ ላይ በስፔን ተሸንፋ ከውድድሩ መሰናበቷ ለአሰልጣኙ ከቡድኑ ጋር መለያየት ምክንያት ሆኗል፡፡

ፖርቹጋል በዓለም ዋንጫው ከኮሎምቢያ እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋር አቻ ስትለያይ ኡዝቤኪስታን እና ክሮሽያን ማሸነፍ ችላለች፡፡

የ52 ዓመቱ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ በ2025 ከፖርቹጋል ጋር የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፋቸው ይታወሳል።

አሰልጣኙ በተደጋጋሚ የ41 ዓመቱን ተጫዋች ክሪስቲያኖ ሮናልዶን በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ማካተታቸው ለትችት የዳረጋቸው ሲሆን፤ ጥሩ ስብስብ ይዘው ደካማ ውጤት በማምጣታቸው ለስንብት ሳይበቁ እንዳልቀረ ተነግሯል፡፡፡

የቤልጂየም ወርቃማ ትውልድን በማባከን የሚወቀሱት ማርቲኔዝ፤ ከፖርቹግል ብሔራዊ ቡድን ጋርም ተመሳሳይ ውድቀት በማስመዝገብ ተሰናብተዋል፡፡

Exit mobile version