አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይና እና ሩሲያ የባህር ኃይል ግዙፍ የጦር መርከቦችን ያሳተፈ የጋራ የባህር ላይ ወታደራዊ ልምምድ ጀምረዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በምስራቅ ቻይና ሻንዶንግ ግዛት የተጀመረው የባህር ላይ ልምምዱ ባለፈው ሰኞ የተጀመረውና ሦስት ምዕራፎች ያሉት የጋራ ልምምድ አካል መሆኑ ተመላክቷል።
በዛሬው ዕለት በቻይና ቺንግዳው ወደብ የተጀመረው የጋራ የባህር ኃይል ልምምድ የአየር መቃወሚያና የጸረ ሚሳኤል ስርዓቶችን እንዲሁም የወታደራዊ መረጃ አሰባሰብና የባህር ላይ ስምሪቶችን ያካተተ መሆኑ ነው የተገለጸው።
በጋራ ወታደራዊ ልምምዱ ላይ አንሻን እና ካይፌንግ የተሰኙት የቻይና ግዙፍ የጦር መርከቦች እንዲሁም ቫርያግ የተሰኘው የሩሲያው የጦር መርከብ እንደሚሳተፍ ተገልጿል፡፡
በዚሁ ወቅት የሁለቱ ሀገራት ወታደሮች የባህር ኃይል መርከቦችን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ ማድረጋቸውን ሽንዋ ዘግቧል፡፡
በምሕረት ደምሴ

