አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባሕር በር ባለቤትነት ሀገራዊ ደህንነትን ለመጠበቅ፣ ኢኮኖሚን ለማሳደግ እና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡
የባሕር በር አለመኖር የሀገርን የንግድ እንቅስቃሴ በመገደብ ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርግ ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴንም በሌሎች ሀገራት መልካም ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
በአንጻሩ የባህር በር ባለቤት የሆኑ ሀገራት የንግድ፣ ጂኦፖለቲካዊና ቀጣናዊ ጥቅምን ለማስከበር በነጻነት የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፤ ይህም በአካባቢያቸው ላይ የሚኖራቸውን የኃይል ሚዛን ለማስጠበቅ ይረዳል፡፡
የባሕር በር ባለቤትነት በሌላ ሀገር ላይ የሚኖር ጥገኝነትን በማስቀረት ቀጣናዊ ተጽዕኖን በመፍጠር ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ ያግዛል፡፡
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ የነበራት ተጽዕኖ እንዲሁም የወደብ ባለቤትነት የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡
በታሪክ አጋጣሚ ልክ ባልነበረ ፖለቲካዊ ውሳኔ የባህር በሯን ካጣች በኋላ የውጭ የንግድ እንቅስቃሴዋ በጎረቤት ሀገራት ወደቦች ላይ የተመሰረተ እንዲሆን አድርጓል፡፡ይህም በየዓመቱ ቢሊየን ዶላሮችን ወጪ እንድታወጣ እያደረጋት ይገኛል፡፡
የ130 ሚሊየን ህዝብ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ በመሆኗ ብሔራዊ ጥቅሟ በጠላት ሴራ ውስጥ እየወደቀ ብዙ ፈተናዎችን ለማስተናገድ ብትገደድም በልጆቿ ትግል ስትሻገራቸው ቆይታለች፡፡
ኢትዮጵያ የምትገኝበት የቀይ ባሕር አካባቢ በዓለም የንግድና የፖለቲካ አሰላለፍ ውስጥ ወሳኝ ቀጣና ነው፡፡
በዚህም የራሷ የባህር በር ቢኖራት በአካባቢው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ተሰሚና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገር ያደርጋታል፡፡
ኢትዮጵያ በየትኛውም ጥያቄዎቿ ብሔራዊ ጥቅሞቿን የሚያስከብርና በጋራ የመልማትን እሳቤ የያዘ በሰላማዊ ውይይት የሚመጣ መልስን ትሻለች፡፡
ኢትዮጵያ የምትጠይቀው በታሪክም በሕግም የራሷ የነበረውን በአንድ ወቅት በግፍ የተነጠቀችውን አካሏን ነው፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ የ130 ሚሊየን ሕዝብ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስንበት፣ እንደ ሀገር የማደግ፣ የመበልጸግ፣ የሕልውና እና ብሔራዊ ጥቅምን የማስከበር የፍትሀዊነት ጥያቄ ነው።
በመልካም ፈቃዱ

