አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለምክክር ጉባዔው ተሳታፊዎች የጉባዔውን ሒደት አስመልክቶ ገለጻ እየሰጠ ነው፡፡
ገለጻው የጉባዔው ተሳታፊዎች በሚያደርጉት የምክክር ሒደት መከተል ያለባቸውን መርሕ እንዲተገብሩ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።
ከዚህ ባለፈም በምክክር ጉባዔው የጋራ መግባባት ላይ መድረስ እንዲቻል ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ከመጪው ሐምሌ 8 ቀን ጀምሮ በሚካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ የሚሳተፉ ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ተወካዮች አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
በይስማው አደራው
የምክክር ጉባዔውን ሒደት አስመልክቶ ገለጻ እየተሰጠ ነው

