Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰወች ቁጥር ከ6 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰወች ቁጥር ከ6 ሚሊየን መሻገሩ ተሰምቷል።

በአለም በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ ተጽዕኖ ውስጥ ከገቡ አገራት ቀዳሚ ሆና ረዘም ላለ ጊዜ የቆየችው አሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰወች ቁጥር ከ6 ሚሊየን በላይ ሆኗል፡፡

ይህም ማለት በአለም በአጠቃላይ በኮሮና ከተያዙ ሰወች ውስጥ ሩብ ያክሉ በአሜሪካ ይገኛሉ።

በቻይና ውሃን ግዛት ከስምንት ወራት በፊት የተከሰተው ወረርሽኙ አሜሪካን ተጽዕኖ ውስጥ ከከተታት ሰነባብቷል።

በትራምፕ አስተዳደር የቀረበው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መቀነስ ሃሳብ የህክምና ባለሙያወች እና በ33 የአሜሪካ ግዛቶች ተቃውሞ ገጥሞታል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ለኮሮና የሚመረመሩ ሰወች ቁጥር መቀነሱም ተነግሯል።

ምንጭ፦ ሲጂቲኤን

Exit mobile version