አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አና ቤርዴ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ቀጣይነት ያለውን የኢትዮጵያ የሪፎርም እንቅስቃሴና የመንግሥትን የትኩረት አቅጣጫ በተመለከተ ለማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም በመጪው የዓለም ባንክ እና የኢትዮጵያ የስትራቴጂያዊ አጋርነት ማዕቀፍ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አና ቤርዴ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ መንግሥት የወሰደውን ጠንካራ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራና አዎንታዊ የኢኮኖሚ ለውጦች አድንቀዋል፡፡
ባንኩ ኢትዮጵያ የሪፎርም አጀንዳዎችንና የረጅም ጊዜ የልማት ግቦችን ለማሳካት በምታደርገው ጥረት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

