Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጉባኤው ለሰላማዊት፣ ዴሞክራሲያዊትና ለተግባባች ኢትዮጵያ መሠረት የሚጥል መግባባት ላይ የሚደረስበት ነው – መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ለሰላማዊት፣ ዴሞክራሲያዊትና ለተግባባች ኢትዮጵያ መሠረት የሚጥል መግባባት ላይ የሚደረስበት ነው አሉ የሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ የሚጀመረውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አስመልክተው ለጉባኤው ተሳታፊዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የታሪካዊ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች የወከላችሁቱን ማህበረሰብ ድምፅና ምኞት ለማስተጋባት ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን የጋራ ዕድልና የወደፊት ዕጣ ፈንታ መሠረት ለመጣል ጭምር በመሆኑ ትከሻችሁ ላይ የወደቀው ኃላፊነት እጅግ ታላቅና ጥልቅ ነው ብለዋል።

በምክክሩ የሚተላለፉ ውሳኔዎች፣ የሚፈጠረው መግባባት እንዲሁም የሚደረሰው ስምምነት ከዚህ የታሪክ ወቅት ባለፈ ዘልቆ የሚቀጥልና ለሰላማዊት፣ ለዴሞክራሲያዊትና ለተግባባች ኢትዮጵያ መሠረት የሚጥል መሆኑን አውስተዋል።

ኮሚሽነሩ በመልዕክታቸው፥ ምክክሩ በጥበብ፣ በጋራ መከባበርና የሕዝብን ጥቅም መሰረት ባደረገ ጽኑ ቁርጠኝነት እንዲመራ እንዲሁም ለመጪው ትውልድ ብሩህ ነገን የሚያሰናዳ እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ ነው ያሉት፡፡

Exit mobile version