Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በይፋ መካሄድ ጀምሯል።

ይህ ታሪካዊ መድረክ ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ መካከል በሚፈጠር ዘላቂ መግባባት እና በጋራ ብሔራዊ ትርክት ላይ እንድትገነባ የሚያስችል ወሳኝና ታሪካዊ የሀገር ግንባታ ሂደት ነው።

ከተጀመረው መርሐ ግብር ጎን ለጎን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች ጋር በመሆን የኮሚሽኑን የአራት ዓመታት ጉዞ የሚያሳይ ልዩ ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል።

ኤግዚቢሽኑ ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ያለፈባቸውን ምዕራፎች፣ ያከናወናቸውን ዝግጅቶች፣ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶችና የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶችን በስፋት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

የጉባኤው በይፋ መጀመር ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሮቿን በራሷ ልጆች ውይይትና የጤረጴዛ ዙሪያ ንግግር ለመፍታት ለጀመረችው ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ነው።

Exit mobile version