Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

አንዳንድ አጋጣሚዎች ከታሪክ ብዕርና ብራና ፊት ያቆማችኋል፤ ከታሪክ ብዕርና ብራና ፊት መቆም ብቻ ሳይሆን ያሻችሁትን የፈቀዳችሁትን መጻፍ እንድትችሉ ብዕርና ብራና ያቀብሏችኋል፡፡
ይህ ዛሬ የምንገኝበት መድረክ ልባም ለሆኑ ሰዎች የታሪክ አጋጣሚን፤ የዕድልን ጠቃሚነት ማዝለቅ ለፈለጉ ሰዎች በብዕርና በብራና ላይ ሀገርን የሚታደግ፣ የሚጠቅም፣ የሚገነባ፣ ለዘመናት የሚታወስ ታሪክ ለመጻፍ ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡
ታሪክ ብራና እና ብዕር ቢያቀብላቸውም ሀገር ከሚጠቅም ይልቅ የሚጎዳ፤ ከሚገነባ ይልቅ የሚያፈርስ፤ ከሚያበለጽግ ይልቅ የሚያደኸይ፤ ከሚያሰፋ ይልቅ የሚያጠብ ታሪክ ጽፈው የሚያልፉ አሉ።
ያ ታሪክ ዛሬ በእኛ እንዳይደገም ከፍተኛ ኃላፊነት ተሰምቶን በታላቅ አክብሮት ልንከውነው የሚገባ እኛና ከእኛ በፊት የነበሩ ሰዎች ያጧቸውን፣ ሊያሳኳቸው ሲገባ ያላሳኳቸውን ጉዳዮች ደግሞ ልጆቻችን እንዳያጡ በታላቅ ኃላፊነት እንድትሰሩ በትህትና ልጠይቃችሁ እወዳለሁ፡፡
ማንም ሳይጎዳ በጋራ መጠቀም የምንችልባቸውን ጉዳዮች አንስተን ፤ለእኔ ሳይሆን ለእኛ፤ ለሰፈሬ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ማለት ከቻልን ይህ ምክክር ፍሬያማ ይሆናል፡፡
እንደዚህ ያለ መድረክ ማዘጋጀት ባለመቻላችን ለዘመናት ዋጋ የከፈሉ፣ የቆሰሉ፣ የሞቱ ኢትዮጵያውያንም ቢያንስ በአጸደ ገነት ሳሉ በሌላ ትውልድ በተሰራ ስራ እረፍት ሊያገኙ ስለሚችሉ ያለፉትን፣ የደከሙትን፣ የሌሉትን እያሰብን አንቺ ትብሽ አንተ ትብስ ብለን ለኢትዮጵያ የሚበጃትን ውጤት እንድናመጣ አደራ ልላችሁ እፈልጋለሁ፡፡
በመልካም ፈቃዱ
Exit mobile version