አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ሰራተኞች ፓርቲ አንዲ በርንሃምን አዲስ መሪ አድርጎ መርጧል፡፡
የገዢው ፓርቲ መሪ ሆነው የተመረጡት በርንሃም ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ያስታወቁትን ኬር ስታርመር በመተካት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንደሚሾሙ ይጠበቃል፡፡
አንዲ በርንሃም የፓርቲው መሪ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራቸውን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ተመራጩ መሪ በስልጣን ዘመናቸው ለማሳካት ያቀዷቸውን አምስት ጉዳዮች ለይተው ማስቀመጣቸው ነው የተገለጸው፡፡
በርንሃም መላው ዩናይትድ ኪንግደምን በእኩልነት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው፥ ሀገሪቱን በጋራ ግቦች ዙሪያ ለማሰባሰብ ቃል መግባታቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው።
አንዲ በርንሃም የኑሮ ወድነትን የሚያቀሉ ርምጃዎችን፣ የሰራተኞችን መብቶች የሚስከብሩ ጠንከር ያሉ ፖሊሲዎች፣ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ማጠናከርና ኢንዱስትሪዎችን ማነቃቃት በትኩረት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
በእመቤት ሲሳይ

