አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል የወባ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል አለ የክልሉ ጤና ቢሮ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ያሲን ሀቢብ እንዳሉት፥ በክልሉ ገቢ ረሱ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች የወባ ትንኝ መከላከያ የኬሚካል ርጭት ዘመቻ ተጀምሯል፡፡
በዞኑ ለ30 ቀናት የሚቆየው ይህ ዘመቻ ከ117 ሺህ በላይ ሰዎችን ከወባ በሽታ እንዲጠበቁ ያስችላል ብለዋል፡፡
የክረምቱ ዝናብ ካበቃ በኋላ ለትንኞች ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ ስፍራዎችን ለማጥፋት ኬሚካልና ለርጭት አገልግሎት የሚውሉ መሳሪያዎች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በዘመቻው ከ43 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን ለኬሚካል ርጭቱ ተደራሽ እንደሚሆኑ የገለጹት ኃላፊው፥ የጤና ባለሙያዎችና የዘመቻ አስፈጻሚዎች አስፈላጊውን ሥልጠና ወስደው ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
በያሲን ኑር

