Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መገናኛ ብዙሀን ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጋለጥ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ጌትየ ትርፌ (ዶ/ር) መገናኛ ብዙሀን ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጋለጥ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል አሉ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሱን ከሀሰተኛ መረጃዎች እንዲጠብቅ እና በኮሚሽኑ ላይ ሙሉ እምነትቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።

ኮሚሽኑ ሐምሌ 8 የተጀመረውን ታሪካዊው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ አስመልክቶ አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጩ እንደሆነ ይፋ አድርጓል።

ገንቢ የሆኑ ሃሳቦችንና ውይይቶችን እንደሚቀበል ያስታወቀው ኮሚሽኑ፤ ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይታለል አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ እንደሚገደድ አስታውቋል።

የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን አስመልክቶ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያነጋገራቸው ጌትየ ትርፌ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የምክክር ሂደቱን በተመለከተ በተለያዩ የማበህራዊ ትስስር ገፆች ከሚተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎች መራቅ ይገባል።

የተደራጁ ቡድኖች የምክክር ሂደቱን ለማጠልሸት ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ አሁንም ምክክሩን ለማጠልሸት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

በዚህም ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን እያደናገሩ ይገኛሉ ብለዋል።

እነዚህ ሀሰተኛ መረጃዎች ተደጋግመው ሊሰራጩ ይችላሉ ያሉት ምሁሩ÷ መረጃዎን አጣርቶ ተገቢውን ምላሽ መሥጠት የሁሉም ባለድርሻዎች ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በተለይም መገናኛ ብዙሀን መሰል ሀሰተኛ መረጃዎችን ቀድመው በማጋለጥ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት፡፡

Exit mobile version