Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ላምሮት የባለተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር ምዕራፍ 23 የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀምራል፡፡
ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተወጣጡ ከ1 ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች ውስጥ የተመረጡ 16 ተወዳዳሪዎች ቅዳሜ የምዕራፍ 23 ውድድራቸውን ይጀምራሉ።
ለ13 ሳምንታት በሚቆየው ውድድር የምድብ አንድ 8 ተወዳዳሪዎች ከኮከብ ባንድ ጋር የውድድር ሙዚቃዎቻቸውን በሁለት ዙር ያቀርባሉ።
ተወዳዳሪዎች በተለያዩ ሳምንታት በራሳቸው፣ በዳኞች እና በተመልካቾች የሙዚቃ ምርጫ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡
ተወዳዳሪዎች በሙዚቃ ባለሙያዎችና በተመልካቾች አጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚዳኙ ሲሆን ÷ በምዕራፉ ፍጻሜ የሚቀሩ 4 ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።
ለፍጻሜ የሚደርሱ አራት ተወዳዳሪዎችም ወደ 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ያልፋሉ።
የፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ውድድር የፊታችን ቅዳሜ በፋና ቴሌቪዥን እና ሌሎች አማራጮች በቀጥታ ሥርጭት ቀን 6 ሰዓት ላይ ይጀመራል።
በለምለም ዮሐንስ
Exit mobile version