Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምክክሩ ያለፉ ችግሮችን በይቅርታ በመሻር አዲስ የወል ትርክት የሚገነባበት ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ያለፉ ችግሮችን በይቅርታ በመሻር አዲስ የወል ትርክት የሚገነባበት ነው አሉ የደሴ ከተማ ምክር ቤት አባላት።
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያነጋገራቸው የደሴ ከተማ ምክር ቤት አባላት እንደገለጹት፤ ሀገራዊ ምክክሩ ሰላሟ የተረጋገጠና ልማቷ የተፋጠነች ሀገር ለመገንባት ትልቅ ሚና አለው።
ከምክክሩ የሚገኙ ውጤቶች መሬት እንዲነኩ እና ስኬታማ እንዲሆኑ ህዝቡን የማስተባበር ሚና እንደሚወጡ አረጋግጠው፤ የምክክር ሂደቱ አሳታፊ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያውያን ያለፉ ዘመናትን ችግሮች በይቅርታ ሽረን አዲስ የወል ትርክት የምንገነባበት አማራጭ መሆኑን ገልጸው፤ ለስኬታማነቱ መተባበር ከሁሉም እንደሚጠበቅ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ የወደፊቷን ጊዜ በመልካም መንገድ ትተልም ዘንድ የተፈጠረ ትልቅ እድል መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፉት ዓመታት የሰበሰባቸውን አጀንዳዎች በስምንት ዋና ዋና አጀንዳ ለይቶ በአሁኑ ወቅት ከ4 ሺህ በላይ ተመካካሪዎች ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ እያካሄዱ መሆኑ ይታወቃል።
እሸቱ ወ/ሚካኤል
Exit mobile version