Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፋና 80 የምዕራፉ 5ኛ ሳምንት ውድድር በመጪው እሁድ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን መልኮች የሚታዩበት ፋና 80 ምዕራፍ አምስት 5ኛ ሳምንት ውድድር በመጪው እሁድ ቀጥሎ ይካሄዳል።
በሳምንቱ የምድብ 1 ስድስት ቡድኖች ይፎካከራሉ።
በዘመናዊ ዳንስ ዘርፍ ነፀብራቅ፣ ቲ ተስፋ፣ ዩኒክ እና ዘውድ ዘመናዊ የዳንስ ቡድኖች ሲወዳደሩ፤ በባህል ውዝዋዜ ዘርፍ ደግሞ ኢትዮ ግዕዝ እና ኬ ሀበሻ የባህላዊ ቡድኖች ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
ዘመናዊ፣ ባህላዊ መባሉን ተወዳዳሪ ቡድኖች ቢጠሩበትም በፋና 80 ሁሉም ተወዳዳሪዎች በስራቸው የኢትዮጵያን መልኮች ነው የሚያሳዩት።
በዕለቱም ስድስቱም ቡድኖች በፋና 80 ውድድር ላይ የሚያቆያቸውን ብቃት እና ፈጠራ በማሳየት ፍልሚያ ደርጋሉ።
በዚህ ሳምንት በባህልም ሆነ በዘመናዊውም የተለያዩ ፈጠራዎች የሚታዩ ሲሆን፤ በተለይም እኔ ብቻ ትክክል የሚል ሀሳብ በዳንስ ይሞገታል፡፡
በዳኞች ሙያዊ ዐይን ተመዝኖ በምዕራፉ አጋማሽ የማይሳተፈው ቡድን ይለያል፡፡
በዚህ እጅግ ማራኪና በከፍተኛ ዝግጅት ቡድኖቹ በሚቀርቡበት ውድድር ላይ ከመድረኩ የሚሰናበተው ቡድን ማን እንደሆነ በመጪው እሁድ ከ9 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው ውድድር ይታወቃል።
በብርኽቲ ማህተም

Exit mobile version