Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል ሰላምን የማጽናት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – አቶ አውሉ አብዲ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰላምን በማጽናት ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው አሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አውሉ አብዲ፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ዜጎች ከስጋት ተላቅቀው በሰላም ወጥተው ሰርተው የሚገቡበትን ሁኔታ በዘላቂነት ለማረጋገጥ የክልሉ መንግሥት ከሕዝብ ጋር ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል፡፡
በተለይም በጫካ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰው፥ በክልሉ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ አካላት ወደ ሰላም ተመልሰዋል ነው ያሉት፡፡
የክልሉ መንግሥት ለሰላም ባለው ፍላጎትና የጦርነት መንገድ ስለማያዋጣ ከታጣቂዎች ጋር ተከታታይ ውይይቶችና ድርድሮች ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
ነገር ግን የቀረቡትን ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች አሻፈረኝ በማለት ክልሉን በሚያወኩና የሕዝብን ሰላም በሚነጥቁ አካላት ላይ ሕግ የማስከበር ሥራ በተጠናከረ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ቀደም ሲል በሰላም እጦት ከልማት ርቀው በነበሩ አካባቢዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ የሕብረተሰቡ ሚና ጉልህ እንደነበር ገልጸው፥ ሰላምን ለማጽናት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በትዕግስት ግዛቸው
Exit mobile version