Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከጣና ሐይቅ ላይ 2 ሺህ 800 ሔክታር የእምቦጭ አረም ማጽዳት ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2018 በጀት ዓመት በጣና ሐይቅ በእምቦጭ ተይዞ የነበረን 2 ሺህ 800 ሔክታር የውሃ አካል ማጽዳት ተችሏል አለ የአማራ ክልል አካባቢና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን፡፡

የባለሥልጣኑ ም/ሃላፊ ተሾመ አግማስ እንዳሉት ÷ በ2018 በጀት ዓመት በአካባቢ፣ በደን እንዲሁም በዱር እንስሳት ጥበቃ እና ልማት ላይ በትኩረት ተሰርቷል፡፡

በአካባቢ ጥበቃ ለ6 ሺህ የልማት ፕሮጀክቶች የይሁንታ ሰርቲፊኬት በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገቡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የወፍ ዋሻ ከጥብቅ ደን ወደ ብሔራዊ ፖርክ እንዲያድግ በቁርጠኝነት መሰራቱን ነው የገለጹት፡፡

በጣና ሐይቅ 2 ሺህ 800 ሔክታር መሬት ላይ የእምቦጭን አረም የማስወገድና አረሙ ወደ ሐይቁ እንዳይገባ የማልማት ሥራ መከናወኑን ጠቁመዋል፡፡

በ2019 በጀት ዓመት ክፍተቶችን በመለየት እና ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ውጤታማ ሥራ ለማከናወን እንደሚሰራ መጥቀሳቸውንም አሚኮ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version