Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወጣቶችን በክህሎት በማብቃት በመዲናዋ ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ ለማሳተፍ እየተሰራ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ወጣቶችን በክህሎት በማብቃት በመዲናዋ ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ ለማሳተፍ እየተሰራ ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር የሚያስገነባውን የስማርት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅት፤ ኮሌጁ በዲጂታሉ ዓለም ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት ያስችላል ብለዋል፡፡
እንዲሁም ሥራ ፈጣሪ ባለሙያዎችን በማፍራት የሀገርን የልማት ጉዞ ለማፋጠን እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡
የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የቦርድ ኃላፊ ሰባስቲያን ብራንዲስ በበኩላቸው፤ ዘላቂ የልማት ጉዞን ለማጠናከር በክህሎት ብቁ የሆኑ ወጣቶችን ማፍራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ድርጅቱ በልዩ ልዩ የልማት መስኮች በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም አንስተዋል።
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 8 የፖሊቴክኒክ ኮሌጆችን መገንባቱ ተመላክቷል፡፡
በሔኖክ ለሜ
Exit mobile version