አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግጭት አደጋ በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 31 ሚሊየን ዩሮ ብድር ሊሰጥ ነው።
በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ለሚገኙ የማኑፋክቸሪንግ፣ አገልግሎት፣ ንግድ ሥራ፣ ኮንስትራክሽን እና የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንተርፕራይዞች ብድሩ ይቀርባል ተብሏል።
የባንኩ የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እና የግሪን ኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ዳይሬክተር ተፈራ በፍቃዱ ብድሩ በተመጣጣኝ የወለድ መጠን ስርዓት እንደሚቀርብ ገልጸዋል።
ለኢንተርፕራይዞቹ የቀረበው ብድር በአነስተኛ የወለድ መጠን በተመረጡ አራት ባንኮች እና አንድ የማይክሮ ፋይናንስ በኩል እንደሚቀርብም አመልክተዋል።
የብድር አቅርቦቱ በሴቶች እና በወጣቶች ለተቋቋሙ ኢንተርፕራይዞች ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን፤ የአውሮፓ ኅብረት እና የጀርመን ልማት ባንክ ብድሩን ማቅረባቸው ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች በዝቅተኛ የወለድ መጠን ብድር ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ከአጋር አካላት ጋር ባለፈው ግንቦት ወር ላይ መፈጸሙ ይታወሳል።

