Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጊፍት ትሬዲንግ በገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የመስሪያ ቦታ ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ፣ 2018፣ ጊፍት ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር በገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የመስሪያ ቦታ መረከቡን አስታውቋል፡፡

ጊፍት ትሬዲንግ 35ኛ ዓመት የምስረታ ኢዮቤልዩ በዓሉን ባከበረበትወቅት እንደገለጸው÷ በኢትዮጵያ ገቢና ወጪ ንግድ ዘርፍ በትኩረት በመስራት ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡

አሁን ላይም ወደ ማኑፋክቸሪንግና አግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመሸጋገር ዝግጅት ማጠናቀቁን ነው ያመላከተው፡፡

ለዚህም በቅርቡ ሥራ በጀመረው ገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በኢንቨስትመንት ለመሰማራት 7 ሺህ 527 ነጥብ 54 ካሬ ሜትር ቦታ መረከቡን ገልጿል።

ቦታው ከጅቡቲ ኮሪደር እና ከሞጆ ደረቅ ወደብ አቅራቢያ የሚገኝ በመሆኑ የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴውን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳልጠው ተመላክቷል።

በኢትየጵያ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግና የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማሳለጥ በበቤንች ሸኮ ዞን የጥቁር አዝሙድ እርሻ መጀመሩ ተጠቅሷል፡፡

ጊፍት ትሬዲንግ በቀጣይ ስድስት ወራት ውስጥ 300 ሄክታር የቡና እርሻ መሬት ተረክቦ ወደ ምርት እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version