Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከኮንጎና አንጎላ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከኮንጎ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮንስታንት ሰርጌ ቡንዳ እና ከአንጎላ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ቴቴ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከኮንጎ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮንስታንት ሰርጌ ቡንዳ ጋር ባደረጉት ውይይት በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በአየር ንብረት ለውጥ መከላከልና መቋቋም ዙሪያ በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው መስኮች ላይ መክረዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ በኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተስማምተዋል።

በተመሳሳይ ጌዲዮን (ዶ/ር) ከአንጎላ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ቴቴ ጋር ባደረጉት ውይይት በሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በተለይም የሕብረቱን አሰራሮች በማጠናከር ዙሪያ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል፡፡

ውይይቱ ከ49ኛው የአፍሪካ ሕብረት ሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ነው የተካሄደው፡፡

Exit mobile version