አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጆርዳን ሄንደርሰን ከብሬንትፎርድ ጋር ተለያይቷል፡፡
የ36 ዓመቱ ተጫዋች በፈረንጆቹ 2025 ከአያክስ አምስተርዳም የፕሪሚየር ሊጉን ክለብ ብሬንትፎርድን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡
ሄንደርሰን ከአንድ የውድድር ዓመት ቆይታ በኋላ በስምምነት ከብሬንትፎርድ ጋር መለያየቱን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
ተጫዋቹ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ቼልሲን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰ ሲሆን እስከ ፈረንጆቹ 2028 የሚያቆየውን ውል ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

