አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 49ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ተጠናቅቋል።
የምክር ቤቱ አባላት ከተለያዩ ተቋማት ጋር የነበሩ ትብብሮችንና የሕብረቱን ግቦች አፈጻጸም በመገምገም አቅጣጫ በማስቀመጥ ነው ጉባኤው የተጠናቀቀው፡፡
የሕብረቱን አቅም ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም የተለያዩ ማዕቀፎች ላይ ከስምምነት የደረሱ ሲሆን፤ ሀገራት ለህብረቱ አጀንዳ 2063 መሳካት የድርሻቸውን እንዲወጡ የምክር ቤቱ አባላት ጫና ማድረግ እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡
አፍሪካ በፋይናንስ ተቋማትና በፖለቲካዊ ተሳትፎዎች በዓለም አቀፍ ተቋማት ሊኖራት በሚገባ የወሳኝነት ሚና የተባበረ ድምጽ ሊኖር እንደሚገባ በጉባኤው ተነስቷል።
በ49ኛው የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የተገኙ የሀገራት ተወካዮች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ለስምምነቶች መተግበር ትኩረት እንዲሰጡም ተጠይቋል።
በአሸናፊ ሽብሩ

