Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአሻራችን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ

አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ ከማልማት ባለፈ ችግኝ በማፍላት፣ በመትከልና በመንከባከብ ሂደት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
ይህ ንቅናቄ በተለይ ለወጣቶችና ለሴቶች የገቢ ምንጭ በመሆን አረንጓዴ ኢኮኖሚን እውን እያደረገ ይገኛል።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሀገራዊ ገጽታን ከማልማትና የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባሻገር ትልቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳን ይዞ መጥቷል።
መርሃ ግብሩ ከተፈጥሮ ጥበቃ ጎን ለጎን የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽል፣ ሥራ አጥነትን የሚቀንስ እና ዘላቂ የገቢ ምንጭን የሚፈጥር ሆኗል።
በሺህ የሚቆጠሩ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች በመገንባታቸው ምክንያት በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡
ወጣቶችና ሴቶች በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው ችግኝ በማፍላት፣ በማከፋፈልና በመሸጥ ገቢ አግኝተዋል።
እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ እና ፓፓያ ያሉ ለምግብ ዋስትና የሚረዱ ፍራፍሬዎችን በማልማት የቤተሰብ ገቢን ማሳደግ ተችሏል።
የተተከሉ ችግኞችን በባለቤትነት በመንከባከብ ሂደት ውስጥ የብዙዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ተደግፏል።
አረንጓዴ አሻራ የደን ሽፋንን ከመጨመርና አካባቢን ከማነቃቃት አልፎ አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ማነቃቂያ ሆኗል።
ይህንን ህዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮ በመቀጠል የተፈጥሮ ሀብትንና የሰውን ህይወት መቀጠል የሁሉም ኃላፊነት ነው።
#ሰኞ ሐምሌ 27፣2018 ዓ.ም ለሚካሄደው በአንድ ጀምበር የ800 ሚሊየን ችግኞች ተከላ ተዘጋጅተዋል?

Exit mobile version