Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብሮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 927 ተማሪዎች አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ገረመው ሁሉቃ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር ውጤታማ የምርምር ስራዎችን እያበረከተ ይገኛል።

በኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት ዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የድርሻውን እየተወጣ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው፤ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የክልሉ መንግሥት ለትምህርት ዘርፉ ውጤታማነት በተለያዩ መስኮች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የተናገሩት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አብዱልአዚዝ ዳውድ (ዶ/ር) ናቸው።

በአሸናፊ ሽብሩ

Exit mobile version