አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 26 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሊባኖስ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሙን ተከትሎ ሀገሪቱ በፍጥነት አዲስ መንግስት እንድትመሰርት ጠይቀዋል።
አዲሱን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የያዙት በጀርመን የሊባኖስ አምባሳደር የነበሩት ሙስጠፋ አዲብ መሆናቸውም ተነግሯል።
ይህንን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ሀገሪቱ በፍጥነት አዲስ መንግስት እንድትመሰርት ጠይቀዋል።
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል በቤሩት የፍንዳታ አደጋው ከተከሰተ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በሀገሪቱ ጉብኝት አካሂደዋል።
በወቅቱም ለሪፖርተሮች እንደገለጹት ÷አዲስ መንግስት በተቻለ ፍጥነት መመስረት አለበት ለዚህም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል።
ኢማኑኤል ማክሮን የሀገሪቱ ፖለቲከኞች ሙስና እና የገንዘብ ብክነትን ለማስቆም ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ግፊት ያሳድራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።
አንድ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን÷ ለአዲሱ ሹመት ከስምምነት ላይ መደረስ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአዳራዳሪነት የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ አዲብ ወደ ስልጣን የመጡት በሀገሪቱ በተከሰተው ፍንዳታ በመቶች የሚቆጠሩ ህይወታቸውን በማጣታቸው እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ በኋላ ነው።
በምንዛሪ ውድቀት ፣ በሥራ አጥነት ቁጥር መጨመር እና ድህነት እያደገ በመጣበት ወቅት በመሆኑ የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መንግስት ብዙ የቤት ስራዎች መሆናቸው ይነገራል ።
በከተማው ወደብ ደህንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ በተከማቸ አሞኒየም ናይትሬት በተፈጠረው ፍንዳታ ቢያንስ 200 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይታወሳል።
ምንጭ፡-ቢቢሲ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

